News Detail
Feb 13, 2024
1.2K views
ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከየካቲት 6–11 /2016 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል። የፈተና አሰጣጡን ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅ ከዩኒቨርስቲዎች ታዛቢዎች መመደባቸውም ተገልጿል ።
ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከነገ የካቲት 6–11 /2016 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና(ፒኤችዲ) የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና በ2015 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በሁሉም የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች ተግባራዊ መደረጉንና በመውጫ ፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ ቁጥር 919/2014 ድንጋጌ መሠረት ፈተናው በዓመት ሁለት ጊዜ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
የሁለተኛ ዙር ፈተናው በ47 የመንግስት ተቋማት በ84 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን በመንግስትና ግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149,145 ተፈታኞች በ204 የፈተና ፕሮግራሞች እንደሚፈተኑ ተናግረዋል።
የመውጫ ፈተና አሰጣጡ ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል በሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ታዛቢዎችን መመደባቸውንም ዶ/ር ኤባ ገልጸዋል ።
የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚው ታዛቢዎቹ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተመለመሉ መሆኑንም ጠቁመዋል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024