News Detail
Feb 12, 2024
987 views
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚተገበሩ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች እውቀት-መር እና አሳታፊ በሆነ አግባብ መተግበር እንዳለባቸው ተገለጸ።
የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚተገበሩ የማህበረሰብ አገልግሎት እና ማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና ለሁሉም ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ጉድኝት የስራ ኃላፊዎች እየሠጠ ነው።
የትምህርት ሚኒስቴር የምርምር እና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች መሪ ሥራ አሥፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን ቢኖር ሥልጠናውን ሲከፍቱ ባስተላለፉት መልዕክት በሀገራችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተደራሽነት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ የተሰራ ቢሆንም ከምርምር እና ማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎች አንጻር የተሻለ ስራ መስራት የሚጠበቅ መሆኑን ገልጸዋል።
ዶ/ር ሰለሞን አክለውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት እና የአቅም ግንባታ ስራዎች በማከናወን ላይ መሆኑን ጠቅሰው የዚህ ስልጠና ዓላማም በተለይም በማህበረሰብ ጉድኝት ላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሻለ አሰራር ስራ እንዲዘረጉና እንዲተገብሩ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ስልጠናው በኮሎራዶ ስቴት ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕ/ር አሠፋ ገብረ-አምላክ የተሰጠ ሲሆን በሀገራችን የሚተገበሩ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ከአለም-አቀፍ ተሞክሮ አንጻር መቃኘት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
በተለይም ለበርካታ ዓመታት በሀገራችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይተገበር የነበረው የማህበረሰብ አገልግሎት ስራ ዩኒቨርሲቲዎች ሰጭ፣ ማህበረሰቡ ግን ተቀባይ የሆነበት አሰራር መፈተሽ እንዳለበት እና ማህበረሰቡ ያለውን አገር-በቀል እውቀት ከግምት በማስገባት ከጽንሰ-ሀሳብ ነደፋ ጀምሮ በማሳተፍ የመፍትሔው አካል ማድረግና በጋራ በመስራት የማህረበሰብ ጉድኝት ስራን በተገቢው መልኩ መተግበር እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
እንደ ፕ/ር አሰፋ ገለጻ ዩኒቨርሲቲዎች የእውቀት ማዕከል ከመሆናቸው አንጻር ለማህረበሰቡ የሚከያከናውኑት አገልግሎት የተለያዩ ለጋሽ ድርጅቶች ከሚያከናውኑት እርዳታ-ነክ ስራዎች ጋር ተያያዥ መሆን የሌለበት ሲሆነ በዩኒቨርሲቲው የሚከናወኑ የማህበረሰብ አገልግሎት እና ጉድኝት ስራዎች እውቀት-መር እና ሙያዊ ስራዎች ላይ አተኩሮ መስራት እንደሚገባም አብራርተዋል፡፡!
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024