News Detail
Aug 29, 2022
2.2K views
የካናዳ መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተጀመረውን እንቅስቃሴ እንደሚደግፍ ገለፀ
የትምህርት ሚኒሰትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የካናዳ መንግስት አምባሳደር ከሆኑት ሚስተር ስቴፋኒ ጆቢን ጋር ነሐሴ 19/2014 ዓም ተወያይተዋል።
በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች ላይ የተነጋገሩ ሲሆን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ መርሃ-ግብርን ተግባራዊ ለማድረግ የካናዳ መንግስት ሊያደርግ ስለሚችለው ድጋፍ እና የበጎ ፈቃደኞች መምህራን ስምሪት ላይ ውይይት ተደርጓል።
የካናዳ አምባሳደር በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተጀመረውን እንቅስቃሴ አድንቀው ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ መርሃግብር ለማሳካትም በኤምባሲያቸው በኩል፣ በካናዳ ዓለምአቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስቴር እና የካናዳ ዩኒቨርሲቲዎች አማካይነት እና በኦታዋ ከተቋቋመው የኢትዮጵያ ግብረሃይል ጋር በመነጋገር እና በማስተባበር የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተለያዩ የለውጥ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።