News Detail

National News
Aug 29, 2022 2.2K views

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነጻነትን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ውስጥ ምሁራን የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ኤታ ዶ/ር ሳሙኤል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነፃነት ተፈፃሚነት ላይ ሁሉም አካላት የበኩላቸውን አስተዋጾ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

የከፍተኛ  ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነጻነት ተግባራዊ መደረግ የተቋማትን የውስጥ አቅም ለማሳደግ ሚናው የጎላ መሆኑንም ገልፀዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነፃነት  ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲደረግ ተቋማቱ የአመራር፣ አስተዳደር፣ አካዳሚያዊ፣ የሰው ኃይል እንዲሁም የገንዘብና ቁሳዊ ሃብት አስተዳደርን በነፃነት እና በተጠያቂነት ለመምራት እንደሚያስችል ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

ለመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነፃነትን ከተጠያቂነት ጋር የሚሰጥ እና የአስተዳደር ስርዓት በአግባቡ  በመዘርጋት፤የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመንግስት አሳሪ አሰራር ደረጃ በደረጃ ተላቀው በነፃነት የሚሰሩበትን ሰርዓት ለመዘርጋት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው፡፡

ተቋማዊ ነጻነት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተልዕኮአቸውን  በተሻለ ሁኔታ ለማሳካት ፣ የመምህራንንም ሙያዊ አስተዋጾ ለማሳደግ እና ኑሯቸውን ለማሻሻል ትልቅ ሚና ያለው በመሆኑ መንግስትም በትኩረት የሚሰራበት መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው አክለዋል።

ተቋማዊ ነጻነት ከመጪው 2015 ዓ.ም ጀምሮ  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መተግበር የሚጀምር ሲሆን በቀጣይ ሁለት ዓመታትም አስር ዩኒቨርስቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡

Recent News
Follow Us