News Detail

National News
Jan 25, 2022 1.2K views

የጋምቤላ ክልል ትምህርት ቢሮ በአማራ ክልል ለተጎዱ ትምህርት ቤቶች መልሶ ግንባታ የሚውል ከ 1.5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ፡፡

የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሴ ጋጃት በአማራ ክልል በህወሐት የሽብር ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች ግንባታ የሚውል 1 ሚሊየን 177ሺ ብር ድጋፍ ለክልሉ ትምህርት ቢሮ አስረክበዋል፡፡
በወረራው ጉዳት ለደረሰባቸው የትምህርት ማህበረሰብ አባላት ደግሞ 350ሺ ብር የሚገመት የአልባሳትና ምግብ ነክ ድጋፎችን አስረክበዋል፡፡
በቀጣይም በ አፋር ክልል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ተመሳሳይ ድጋፍ እንደሚደረግ የጋምቤላ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሴ ጋጄት ተናግረዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር በአማራ እና አፋር ክልሎች በህወሐት የሽብር ቡድን ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለመገንባት ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር በትብብር እየሰራም ይገኛል፡፡
የጋምቤላ ትምህርት ቢሮ ድጋፍ የትብብሩ አንዱ አካል ሲሆን ሌሎች ክልሎችም ይህንን አርዓያ በመከተል የትምህርት ቤቶችን መልሶ ግንባታ በመደገፍ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡
Recent News
Follow Us