News Detail

National News
Jan 26, 2022 1.1K views

Professor Berhanu Nega discussed with Swedish Ambassador to Ethiopia Hans Henrik on the rebuilding of damaged schools due to war in Northern part of Ethiopia

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የስዊዲን አምባሳደር ክቡር ሃንስ ሄንሪክ ጋር በወደሙ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸውም የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ የስዊዲን መንግስት ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ በርካታ ጥራት ያላቸው ትምህርት ቤቶችን ገንብቶ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን አስታውሰው በአሁኑ ወቅት በአሸባሪው የህውሃት ቡድን የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ደረጃቸውን በጠበቀ ሁኔታ መልሶ ለመገንባት መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
የስዊዲን አምባሳደር ክቡር ሃንስ ሄንሪክ በበኩላቸው አገራቸው የትምህርት ተቋማትን በጥራት መልሶ ከመገንባት አንፃር ወደፊት ምላሽ እንደምትሰጥ ገልፀዋል፡፡
በአገራችን እስከአሁን ድረስ የሲዊዲን መንግስት ከ6000 በላይ ጥራታቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶችን መገንባቱ ይታወቃል፡፡
Recent News
Follow Us