News Detail
Nov 11, 2025
725 views
34ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ዛሬ በአዳማ ከተማ ተጀመረ፤
'ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም'' በሚል መሪ ቃል በተጀመረው ጉባዔ የ2017 የትምህርት ልማት ዘርፍ አፈጻጸም ይገመገማል።
ጉባዌው በ2018 የትምህርት ዘመን እቅድ ላይ ውይይት በማድረግ ለተሻለ አፈጻጸም የሚያግዙ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ በሚገኘው ሀገር አቀፍ ጉባዔ የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በተጨማሪም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ፣የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፣የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዚዳንቶችና አጋሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
Recent News
የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተደረገላቸው አቀባበል
Dec 20, 2025
Dec 15, 2025
Nov 18, 2025