News Detail
Aug 31, 2020
643 views
የመምህርነት ሙያ ተመራጭና ተወዳጅ ሙያ ለማድረግ ይሰራል፡- ትምህርት ሚኒስቴር
በየደረጃው የሚገኙ የሚኒስቴሩ ሰራተኞች እና አመራሮች በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፉ የ10 አመት እቅድ ላይ ውይይት እያደረጉ ነው፡፡
በየደረጃው የሚገኙ የሚኒስቴሩ ሰራተኞች እና አመራሮች በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፉ የ10 አመት እቅድ ላይ ውይይት እያደረጉ ነው፡፡
በውይይቱ በትምህርት ስርዓቱ የመምህርነት ሙያ ከምልመላ ጀምሮ ችግሮች እንዳሉበት ተነስቷል፡፡
መምህርነትን መርጠውና ፈልገው የሚመጡ ባለሙያዎች በሌሉበት የትምህርት ጥራትን ማሻሻል አስቸጋሪ መሆኑም ተብራርቷል፡፡
ሙያው የሚጠበቅበትን ተልዕኮ ለማሳካት የሙያው ባለቤት የሆኑ መምህራን በአግባቡ ሊሰለጥኑና የሙያውን ግዴታ ለመወጣት በሚያስችል ደረጃ ሊዘጋጁ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
መምህርነትን ተመራጭ የሙያ መስክ ለማድረግ የመምህራንን ብቃትና ተነሳሽነት ማሳደግ፣ የስልጠና ስርዓቱን፣ የኑሮ፣ የስራና የገቢ ሆኔታን በማሻሻል የሙያውን ክብርና ደረጃ ማሳደግ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡
በዚህም የመምህርነት ሙያ ተመራጭና ተወዳጅ ሙያ ለማድረግ በቀጣይ አስር ዓመታት በትኩረት ለመስራት መታቀዱ ተገልጿል፡፡