News Detail

National News
Oct 06, 2021 577 views

ትምህርት ሚኒስቴር “ የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት" የንቅናቄ ዘመቻን ተቀላቀለ።

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች እና ሠራተኞች በ ምዕራቡ አለም ያለውን የተዛባ አመለካከት ለማሳወቅ“ የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት" የንቅናቄ ዘመቻን በይፋ ተቀላቅለዋል።
መርሃ ግብሩን የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታዎቹ ገረመው ሁሉቃ (ዶ/ር ) እና ወ/ሮ ሁሪያ አሊ አሻራቸውን በማኖር አስጀምረዋል፡፡
ዘመቻው በነጩ ቤተ መንግስት ያለው የተዛባ መረጃ እንዲጠራና ትክክለኛ መረጃ እንዲኖር መልእክት ለማስተላለፍ መሆኑም ተገልጿል።
የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ ገረመው ሁሉቃ(ዶ/ር) የነጩ ቤተመንግስት በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያለውን የተዛባ መረጃ ትክክል አለመሆኑን ለማሳወቅ የሚደረግ ዘመቻ ነው ብለዋል፡፡
ዘመቻው የተቀረው ማህበረሰብ ትክክለኛ መረጃ እንዲይዝ ለማስቻል እንደሚረዳም ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
የነጩ ፖስተ ጎርፍ ለነጩ ቤተ-መንግሰት የንቀናቄ ዘመቻ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ብሎ የፈረጀውን ቡድን ከመንግስት እኩል ማየት አግባብ አለመሆኑን መልዕክተ ለማስላለፍ ጭምር መሆኑን በመርሀ ግብሩ ላይ ተገልጿል።
ከዚህ ቀደም የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ) ነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተ መንግስት ዘመቻ ድምፃቸውን ማሰማት ላልቻሉ ከ3ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ድምፅ የያዘ ነው ማለታቸው ይታወሳል።
Recent News
Follow Us