News Detail
Oct 06, 2021
567 views
በኮቪድ ፕሮቶኮል አተገባበር ላይ በ150 ትምህርት ቤቶች የተካሄደ ጥናት ይፋ ሆነ።
ትምህርት ሚኒስቴር በCOVID-19 ምክንያት ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶች ዳግም ከተከፈቱ በኋላ ወረርሽኙ የመከላከልና የመቆጣጠር መመሪያ አተገባበሩን ያለበትን ደረጃ ለማውቅ በ150 ትምህርት ቤቶች ላይ ያደረገውን ጥናት ይፋ አድርጓል።
የትምህርት ሚኒስቴር ጥናቱን ያካሄደው Education Development Trust ከሚባል ድርጅት ጋር በመተባበር ነው።
ጥናቱ በCOVID-19 ምክንያት ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶች ዳግም ከተከፈቱ በኋላ ወረርሽኙ የመከላከልና የመቆጣጠር መመሪያ አተገባበሩን ያለበትን ደረጃ ለማመልከት የተካሄደ ነው።
በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬት ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ታዬ ግርማ ጥናቱ ተማሪዎች ዳግም ወደ ትምርት ገበታ ከተመለሱ በኋላ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመከላከል ትምህርታቸውን ለማስቀጠል የሚያስችሉ መፍትሄዎችን የጠቆመ መሆኑን ተናግረዋል።
ትምህርት ቤቶች ዳግም ሳይከፈቱ በፊት የCOVID-19 ወረርሽኝ ምክንያት የመማር ማስተማሩ ሂደት እንዳይቋረጥ በወቅቱ ያልተዳሰሱትን ትምህርቶች ለ45 ቀናት በተለያዩ የሚዲያ አግባቦችን በመጠቀም ለተማሪዎች ተደራሽ ሲደረግ እንደነበረ ጠቅሰዋል፡
ጥናቱ የተካሄደው በዘጠኝ ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ሥር የሚገኙ በናሙናነት በተመርጡ 150 ትምህርት ቤቶች ላይ ነው።
በአንዳንድ ክልሎች ዳግም ትምህርት ቤቶች ከተከፈቱ በኋላ ያለው የተማሪዎች ምዝገባ ከበፊቱ በተነፃፃሪ መቀነሱን፣ ፕሮቶኮሉን በተማሪዎች ብዛት መሠረት በመማሪያ ክፍል ውስጥ ያለመተግበር፣ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ወደ ትምርት ገበታ ሳይመለሱ የመቅረት፣ የመምህራን እጥረት መታየቱን፣ የCOVID-19 ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር ፕሮቶኮልን በአግባቡ ተግባራዊ አለማድረግ ችግሮች በጥናቱ ተለይተዋል፡፡
ጥናቱን ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከክልልና ሁለቱም የከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች፣ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ከትምህርት ልማት አጋር ደድርጅቶች የተውጣጡ የዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተወያይተውበታል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024