News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Oct 06, 2021 1K views

"ሁለንተናዊ የስፖርትና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የመስራትና የመፈጸም አቅምን ያጎለብታል"- ገረመው ሁሉቃ (ፒ ኤች ዲ)

ሁለንተናዊ የስፖርትና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጤናን ከማስጠበቅ ባሻገር የመስራትና የመፈጸም አቅምን እንደሚያጎለብት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ገረመው ሁሉቃ (ፒ ኤች ዲ) ተናገሩ።
ሚኒስትር ዴኤታው ይህን ያሉት የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞች የስፖርት ለሁሉም መርሃ ግብር ባካሄዱበት ወቅት ነው።
ሚኒስትር ደኤታው ስፖርት ለሁሉም የመስራት አቅምንና ምርታማነትን ከፍ በማድረግ ውጤታማነትን ይጨምራል ብለዋል።
የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በየሶስት ወሩ በስፖርት ለሁሉም የሚያደርጉት ሁለንተናዊ የስፖርት እንቅስቃሴም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በእለቱም በአመራርና በሰራተኞች መካከል የተለያዩ የመዝናኛ ውድድሮች ተካሂደዋል።
ሚኒስቴር መ/ቤቱ የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን በየዓመቱ በሚያካሂደው የስፖርት ለሁሉም ውድድር ላይ ከ2006 ዓም ጀምሮ በተከታታይ ዓመታት ከሴክተር መስሪያ ቤቶች አንደኛ በመውጣት የአጠቃላይ አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል።
Recent News
Follow Us