News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Oct 06, 2021 546 views

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ከሶስት ሺ በላይ የሚሆኑ የተለያዩ መጽሓፍቶችን ለትምህርት ሚኒስቴር ድጋፍ አደረገ፡፡

የጅማ ዩኒቨርሲቲ በ አራት ኪሎ አካባቢ እየተገነባ ላለው ዘመናዊ የህዝብ ቤተ-መጽሐፍት ከሶስት ሺ በላይ የሚሆኑ የተለያዩ መጽሓፍቶችን ለትምህርት ሚኒስቴር አስረክቧል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ(ዶ/ር ኢንጅ) የሚገነባው የህዝብ ቤተ-መጽሐፍት ከአፀደ ህፃናት ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ድረስ ለሚማሩና ማንበብ ለሚፈልጉ ትልቅ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ግዙፍ ፕሮጀክት በመሆኑ የመፅሀፍት ድጋፉ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ይህንን ትልቅ የህዝብ ቤተ-መጽሐፍት ወደ ስራ ለማስገባት በሚደረገው ጥረት የጅማ ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ተግባር አርዓያነት ያለው መሆኑን ጠቅሰው ሌሎችም ይህንን ተግባር እንዲከተሉም ጠይቀዋል፡፡
የጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ቀነኒሳ ለሚ(ዶ/ር ) ዩኒቨርሲቲው በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንዳለ እና የመጽሐፍት ድጋፍም አንዱ አካል መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ፕሮጀክቱም የሚያነብና የሚመራመር ትውልድ ለመፍጠር ትልቅ አስዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት ለህዝብ ቤተመጽሐፍት አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ መጽሐፍቶች እየተሰባሰቡ ይገኛል፡፡
Recent News
Follow Us