News Detail
Mar 29, 2021
2K views
የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከግማሽ በላይ ተማሪዎች ከ350 በላይ ማምጣታቸው ተገለፀ።
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን በተመለከተ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።
የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዲላሞ ኦተሪ(ዶ/ር) የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተመዝጋቢ፣ በተፈታኝም እንዲሁም በውጤትም ደረጃ ከፍተኛ መሆኑ ገልፀዋል።
ፈተናውን ከወሰዱ አጠቃላይ ተፈታኞች ውስጥ 55.7 ፐርሰንቱ ከ 350 በላይ አምጥተዋል።
በመግለጫው የፈተና ውጤት ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም ከ 600 በላይ ያመጡ ተማሪዎች 702 መሆናቸው ተገልጿል።
የዓመቱ ከፍተኛ ውጤትም 669 ሆኖ መመዝገቡን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል ።
ተማሪዎችም ውጤታቸውን በፈተናዎች ኤጀንሲ ድረገፅ እንዲሁም በአጭር የፁሁፍ መልዕክት 8181 የፈተና መለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ከነገ ጀምሮ ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።
ወደ ዪኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜን እና ማለፊያ ነጥብን በተመለከተ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየተሰራ መሆኑም ዳይሬክተሩ በመግለጫው አስታውቀዋል።
Recent News
Sep 02, 2025
Aug 29, 2025
Aug 28, 2025
Aug 23, 2025