News Detail
Mar 22, 2021
716 views
ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በዚህ አመት 200 የአካቶ ትምህርት መስጫ ማዕከላት ተቋቁመዋል
የትምህርት ሚኒስቴር በልዩ ድጋፍ መስጫ ማዕከላት ዙሪያ ለርዕሳነ መምህራንና ተዘዋዋሪ መምህራን ስልጠና ሰጥቷል።
በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎችን ተደራሽነት ለማረጋገጥ የትምህርት ሚኒስቴር በዚህ አመት 200 የአካቶ ትምህርት ድጋፍ መስጫ ማእከላትን አቋቁሟል።
ማዕከላቱ እስከ 35 የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ናቸው። ስልጠናው የተሰጠው ርዕሳነ መምህራንና ተዘዋዋሪ መምህራንን ማዕከላቱን በአግባቡ በማደራጀት በተገቢው መንገድ መጠቀም እንዲችሉ ለማድረግ ነው።
የልዩ ድጋፍና አካቶ ትምህርት ዳይሬክተር አቶ ተኽላይ ገ/ ሚካኤል በአገሪቱ አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሁሉም ህጻናት የመማር መብታችው እንዲረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ቢሆንም አሁንም የአካል ጉዳተኛ ህጻናት የትምህርት ተሳትፎ በዝቀተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል።
ፍትሀዊ የትምህርት ተደራሽነት ማረጋገጥ የሁሉም የትምህርት ስራ ባለድርሻዎች መሆኑን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ በተለይም ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት በመላክ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
የትምህርት ፍትሀዊነትን በማረጋገጥ የአካል ጉዳተኞችን የትምህርት ተሳትፎ ለማጎልበት ትምህርት ሚኒስቴር የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024