News Detail
Jan 22, 2021
477 views
የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትን የሚያስተባብር ምክትል ርዕሰ መምህር በሁሉም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲኖር የሚያስችል የአደረጃጀት መመሪያ እየተዘጋጀ ነው
የትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሳና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ፕሮግራምን ውጤታማ ለማድረግ በሚረዱ የአሰራርና የአደረጃጀት ለውጦች ላይ ከክልል ትምህርት ቢሮ አመራሮችና የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ምክክር እያካሄደ ነው፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ጌታሁን ጋረደው (ፒ ኤች ዲ) የተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ያሉበትን ችግሪች በመፍታት ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል አሰራርና አደረጃጀት ከፌደራል ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ እንዲኖር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በሁሉም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በጀማሪ ምክትል ርዕሰ መምህር ደረጃ አመራር ለመመደብ የሚያስችል የአደረጃጀት መመሪያ እየተዘጋጀ ነውም ብለዋል፡፡
በመደበኛ ትምህርት ብቻ የሚፈለገውን ለውጥ ማምጣት ስለማይቻል ይህንን ጉድለት ለመሙላት የሚያስችል የጎልማሳና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ፕሮግራምን ውጤታማ በሆነ መንገድ በመተግበር የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገልጧል፡፡
የአሰራርና የአደረጃጀት ስትራቴጂና መመሪያዎች በምክክር መደረኩ የሚገኙ ግብዓቶችን ከተካተቱባቸው በኋላ በሚመከተው አካል ሲፀድቁ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ ይደረጋሉ ተብሏል፡፡