News Detail

National News
Jan 20, 2021 477 views

በትግራይ ክልል በልዩ ልዩ ምክንያቶች ቷቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስጀመር እየተሰራ ነው

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ባለሙዎች በትግራይ ክልል በቀጣይ ትምህርት ለማስጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከክልሉ ጊዜያዊ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር መክረዋል፡፡

ለናሙናነት በተካሄዱ የመስክ ምልከታዎች እንደተረጋገጠው በክልሉ የሚገኙ የትምህርት መሠረተ-ልማትና ግብዓቶች በህወሃት የጥፋት ቡድን ጉዳት እንደደረሰባቸውና እንደተዘረፉ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የመማር-ማስተማር ሥራው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ነበረበት እንዲመለስ የክልሉ መንግሥትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ክትትል የሚያደርግ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ሁሪያ አሊ አረጋግጠዋል፡፡

Recent News
Follow Us