News Detail
Dec 24, 2020
858 views
በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተገነባው ደባርቅ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጠናቀቀ
በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ሙሉ ወጪ የተገነባው በአማራ ክልል የሚገኘው ደባርቅ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታው ተጠናቋል።
በትምህርት ቤቱም በቀጣይ ወር ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጿል ፡፡
በትምህርት ቤቱም በቀጣይ ወር ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጿል ፡፡ትምህርት ቤቱ በ13 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን 18 መማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መፅሀፍት፣ ቤተ ሙከራዎች፣ የአስተዳደር ህንፃ፣ መጸዳጃ ቤትና ክሊኒክ ያሟላ ነው፡፡
የትምህርት ቤቱ መገንባት በከተማው የሚታየውን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ችግር የሚፈታ መሆኑ ተገልጿል ፡፡
ምንጭ- አማራ ክልል ትምህርት ቢሮ