News Detail
Dec 07, 2020
682 views
የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀንን አከበሩ።
የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች 15ኛውን የብሄር ብሄረሰብና ህዝቦች ቀን "እኩልነት እና ህብረ ብሄራዊ አንድነት ለጋራ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል አክብረዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዬን ማቲዬስ የዘንድሮው ክብረ ባዕል እኩልነትን እና ህብረ ብሄራዊነትን አጉልቶ የሚያሳይ ነው ብለዋል።
በዝግጅቱም በወቅታዊ እና ሀገራዊ ጉዳይ ላይ የተለያዩ ሰነዶች ቀርበው ውይይት የተካሄደባቸው ሲሆን ሰራተኛውም በውይይቱ የጋራ አቋም እና ግንዛቤ እንዲይዝ ተደርጓል።
በፕሮግራሙ መንግስት ህብረብሄራዊነትን እና የሀገርን ሰላም ለማስጠበቅ እየወሰደው ያለው እርምጃ ትክከለኛ እና የሀገርን ደህንነት ያረጋገጠ መሆኑም ተገልጿል።