News Detail

National News
Oct 30, 2020 913 views

ትምህርትን ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑ ተገለፅ።

የትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የመጀመሪያው ሩብ አመት ሪፖርት ለጠቅላይ ሚኒስተር ጽህፈት ቤት ቀርቦ ምለሽ ተሰጠበት፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የሴክተር መስሪያ ቤቶች የእቅድ አፈጻጸም ክትትል እና ግምገማ ቡደን በትምህርት ሚኒስቴር በመገኘት በሩብ አመቱ አፈጻጸም ዙሪያ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትምህርትን ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር እየሰራው ያለው ስራ አበረታች እና ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ተጦቁሟል፡፡

በተቋሙ ውስጥም ያለው አደረጃጀት እና የቡድን አሰራር የተቃላጠፈ እና ውጤታማ መሆኑንም የክትትል ቡድኑ ገልጿል፡፡

የሚኒሰቴር መስሪያ ቤቱ የሩብ አመት አፈጻጸም አበረታች እና ለሌሎች ሴክተር መስሪያ ቤቶችም አርያ ሊሆን እንደሚችል ቡድኑ አስታውቋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የሩብ አመት እቅድ አፈፃፀምን ለሚዲያዎች ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

Recent News
Follow Us