News Detail

National News
Oct 28, 2020 545 views

በአፋር ክልል በስራ ላይ እያሉ ህይወታቸውን ላጡ የትምህርት ሚንስትር ሰራተኞች ሽኝት ተደረገ።

የትምህርት ሚኒስቴር ባልደረባ የነበሩ ሁለት ሰራተኞች በአፋር ክልል በስራ ላይ ሳሉ ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸውን አጥተዋል።

የሰራተኞቹ አስክሬን ከአፋር ክልል ዛሬ ወደ አዲስ አበባ የገባ ሲሆን በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች አቀባበል ተደርጎላቸው ወደ የአካባቢያቸው ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ(ፒ ኤች ዲ) በሽኝቱ ላይ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን በመመኘት የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም በሰራተኞቹ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለስራ ባልደረቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ይመኛል።

Recent News
Follow Us