News Detail
Oct 24, 2020
770 views
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ በመጪው ሳምንት ይጀመራል፡፡
የ2012 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ከጥቅምት 16 እስከ 30 /2013 ዓ.ም በየትምህርት ቤቶቹ እንደሚካሄድ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የፈተና ምዝገባ ሂደቱን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማካሄድ በተዘጋጀው ሶፈትዌር “Enrollment Kit” ላይ ምዝገባ ለሚያከናውኑ የአይ ሲ ቲ ባለሙያዎችና የፈተና ክፍል አስተባባሪዎች በየክልል ከተሞች ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።
የ2012 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በኦላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡