News Detail
Oct 09, 2020
520 views
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ(ፒ ኤች ዲ) በተለያዬ ትምህርት ቤቶች የመስክ ምልከታ አካሄዱ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ(ፒ ኤች ዲ) በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልልሎች የትምህርት ቤቶችን ዝግጅት ተመልክተዋል።
ሚኒስትሩ በ አዳማ እና በሰበታ ያሉ ትምህርት ቤቶችን የተመለከቱ ሲሆን በ አዳማ በ 1.2 ሚሊየን ብር የተገነባውን እና ሌሎች አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዝግጅቶችን ተመልክተዋል።
በተመሳሳይ በሰበታ ከተማ በ ህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነቡ ትምህርት ቤቶችን እና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዝግጅትን በከተማዋ ባሉ የተለያዬ ትምህርት ቤቶች ጎብኝተዋል።
አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶችም በህብረተሰቡ ተሳትፎ እና በድርጅቶች ድጋፍ መሰራታቸውም ታውቋል።
ሚኒስትሩም ተዘዋውረው በተመለከቷቸው ትምህርት ቤቶች እየተሰሩ ያሉት ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን እና ትምህርቱን ለማስቀጠል አጋዥ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ ክልሎች ያሉ ትምህርት ቤቶች ያሉበትን ደረጃ ተዘዋውረው እየተመለከቱ ነው