News Detail
Oct 09, 2020
622 views
ትምህርት ሚኒስትሩ በሰበታ ከተማ የተገነባው ዲማ ማኞ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስመረቁ።
ትምህርት ቤቱ በኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ካምፓኒ ( ኮካኮላ) በ 7.5 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ ነው። ትምህርት ቤቱ 8 መማሪያ ክፍል፣ 1 ቤተ መፅሀፍት፣ እጅ መታጠቢያ፣ ሽንት ቤት እንዲሁም በቂ የመቀመጫ ወንበሮች የተሟሉለት ነው።
ሚኒስትሩም ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ኩባንያ ለሰራው ስራ አመስግነውበሀገር ውስጥ የተሰማሩ ሌሎች ድርጅቶችም በትምህርት ቤት ግንባታና በውሃ አቅርቦት እገዛ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
የሰበታ ከተማ ከንቲባ አቶ ብርሃኑ በቀለ ከ ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ኩባንያ ሃላፊ ዊሊያም ዴሪ የትምህርት ቤቱን ቁልፍ ተረክበዋል።
ትምህርት ቤቶቹ በከተማ አስተዳደሩ እና በባለሀብቶች እንዲሁም በህብረተሰቡ የበጎ ፈቃድ መርሀ ግብር የተገነቡ መሆኑም ተገልጿል።
የሰበታ ከተማ ከንቲባ አቶ ብርሃኑ በቀለ ከኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ኩባንያ ሃላፊ ዊሊያም ዴሪ የትምህርት ቤቱን ቁልፍ ተረክበዋል።
በትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ የተመራ ልዑክ በሰበታ ከተማ አስተዳደር በ2013 በጀት አመት የኮሮና ቫይረስን እየተከላከሉ ትምህርት መጀመር የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት እና የማስፋፊያ ስራዎች እየተጎበኘ ይገኛል።