News Detail

National News
Oct 16, 2025 40 views

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ አዲስ ከተሾሙት የሀንጋሪ አምባሳደር ጋር ተወያዩ።

የትምህርት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙትን የሀንጋሪ አምባሳደር አቲላ ቶዝን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል ።
በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ እና ሀንጋሪ በትምህርቱ ዘርፍ በትብብር ሲሰሩ መቆየታቸውን አንስተዋል።
በተለይም በ2023 በትምህርት ሚኒስቴርና በሀንጋሪ ኢምባሲ በኩል የተፈረመውን የነጻ የትምህርት እድል ስምምነት በተመለከተ እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት አንስተው ተወያይተዋል።
በዚሁ ጊዜ ክቡር ሚኒስትሩ ይህንን የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሰነድ አስተካክሎ ለሀገራችን ልማትና ኢኮኖሚያዊ እድገት ጠቃሚ በሆኑ የትኩረት መስኮች በተለይም በፔትሮ ኬሚካል፣ በኒውክለር ሳይንስ፣ በማዕድን ልማት ፣ በቱሪዝምና ባህል እንዲሁም በሀገራችን በማይሰጡ የትምህርት ፕሮግራሞች ላይ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ የነጻ የትምህርት እድል መስጠት በሚያስችል መልኩ ማሻሻልና መፈራረም እንደሚገባ ለአዲሱ አምባሳደር አብራርተውላቸዋል።
በኢትዮጵያ አዲሱ የሀንጋሪ አምባሳደር አቲላ አቶዝ በበኩላቸው ሚኒስትሩ ባቀረቡላቸው የሀገራችንን ልማትና ኢኮኖሚን በሚደግፉ አዳዲስ የትምህርት መስኮች ላይ ትብብር ለማድርግ በመሰረተ ሀሳብ ደረጃ ስምምነታቸውን ገልጽዋል።
በዚህም በሁለቱ ሀገራት መካከል የተጀመረውን የመግባቢያ ስምምነት ለማሻሻል ከሀገራቸው የሥራ ኃልፊዎች ጋር በመነጋገር እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ሁለቱ አካላት በውይይታቸውም ከዚህ በፊት የነበረውን የመግባቢያ ስምምነት ለማሻሻልና በተለያዩ አዳዲስ የትምህርት መስኮች የነጻ የትምህርት እድል ለማመቻቸት ከስምምነት ላይ ደረሰዋል።
Recent News
Follow Us