News Detail

National News
Oct 16, 2025 30 views

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት የተማሪዎች ውጤት እየተሻሻለ መምጣቱን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጋምቤላ ክልል "የትምህርት ፍትሃዊነትና ጥራት ለትውልድ ግንባታ" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ክልል አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ላይ ተሳትፈዋል።
በዚሁ ጊዜ ባደረጉት ንግግር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በትምህርት ዘርፉ በተተገበሩ የሪፎርም ተግባራት በተማሪዎች ውጤት ላይ መሻሻሎች እየታዩ መምጣታቸው አብራርተዋል።
አክለውም እንደ ሀገር ዘላቂ ልማትና እድገት እንዲረጋገጥ ጥራት ያለው ትምህርትን ተደራሽ በማድረግ በራሱ የሚተማመን ዜጋ መገንባት ያስፈልጋል፤ ለዚህም በትምህርት ዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በጋምቤላ ክልልም በተማሪዎች ውጤት ላይ ለውጥ መኖሩን ጠቅሰው ለውጡን ይበልጥ ለማጠናከር አመራሩ በላቀ ቁርጠኝነት እንዲሰራ አስገንዝበዋል።
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ዓለሚቱ ኡሞድ በትምህርት ሽፋን የተሻለ ስኬት መመዝገቡን ገልጸው ጥራትን በማረጋገጥ ረገድ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ክልሉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በክልሉ የትምህርት ተሳትፎንና ጥራትን ለማረጋገጥ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ የሚሰራ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
Recent News
Follow Us