News Detail

National News
Oct 17, 2025 32 views

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ከአለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ዋና ምክትል ኃላፊ ጋር ተወያዩ፤

የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታዋ የአለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ምክትል ኃላፊ ሙቲንታ ሀምባይን (ዶ/ር) በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ሁለቱ አካላት በቀጣይ የኢትዮጵያ የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።
በዚሁ ጊዜ ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ የኢትዮጵያ መንግሥት ለትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብር በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለመርሃ-ግብሩ የሚመድቡት በጀት አየጨመረ መምጣቱንና ህብረተሰቡም ለመርሃ-ግብሩ ውጤታማነት የሚያደርገው ተሳትፎ በየጊዜው እያደገ የመጣ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የአለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ሙቲንታ በበኩላቸው የኢትዮጵያ የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብር በአፍሪካ ትልቁና ቀዳሚ መሆኑን ጠቅሰው በቅርቡ በተካሄደው አለም አቀፍ የትምህርት ቤት ምገባ ጥምረት ስብሰባ ላይ እውቅና የተሰጠውና በአርዓያነት የሚጠቀስ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት ለትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብር መተግበር ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየተሰሩ ባሉ ሥራዎች ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡
Recent News
Follow Us