News Detail

National News
Oct 20, 2025 55 views

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጲያ UNFPA ተወካይ ጋር ተወያዩ።

የትምህርት ሚኒስትሩ በኢትዮጲያ የUNFPA ተወካይ Mr. Sk Kouameን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በዚሁ ጊዜ በኢትዮጲያ UNFPA ተወካይ የሆኑት Mr. Sk Kouame UNFPA በሴቶች ትምህርት በተለይም ለሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ግብዓቶችን በማቅረብ እየሰራ መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይም ይህንን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለክቡር ሚኒስትሩ አብራርተውላቸዋል።
UNFPA ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከሌሎች ጋር በመተባበር የሴቶችን የትምህርት ሁኔታ በማመቻቸት ረገድ የበለጠ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚፈልጉም ገልጸውላቸዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ በበኩላቸው UNFPA ውስን በሆነ መልኩ ለሴት ተማሪዎች ሲያደርግ የነበረውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።
አክለውም በቀጣይ ከእንዲህ ዓይነት ውስን ድጋፎች ተላቆ በራስ አቅም የሴቶችን ንጽህና መጠበቂያ በማምረት ለኢትዮጵያም ብሎም ለአፍሪካ የሚጠቅም ሥራ መስራት እንደሚገባ ለካንትሪ ዳይሬክተሩ አብራርተውላቸዋል።
Recent News
Follow Us