News Detail

National News
Oct 19, 2025 39 views

የማጠናከሪያ ትምህር በዕቅድና በትኩረት እንዲመራ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ

 

የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት አየለች እሸቴ ከክልልና ከከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በበይነ መረብ ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት በአጠቃላይ ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ በተለይም ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርትን በዕቅድና በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል።
የተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ መምህራን፣ የትምህርት ቤት አመራሮች፣ ወላጆች እንዲሁም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተማሪዎች ጊዚያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ከወዲሁ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ክብርት ወ/ሮ አየለች አስገንዝበዋል።
‎የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በበኩላቸው የማጠናከሪያ ትምህርት ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል ጠቀሜታው የላቀ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።
‎የትምህርት ፕሮግራሞች ጥራትና መሻሻል መሪ ስራ አስፈጻሚ ዩሀንስ ወጋሶ(ዶ/ር) የማጠናከሪያ ትምህርትን በተመለከተ መነሻ ስትራቴጂ እቅድ ያቀረቡ ሲሆን የተያዘው ግብ እንዲሳካ ከወዲሁ የዕቅድ ክትትልና ድጋፍ ሥራዎች ሊጠናከሩ ይገባል ብለዋል።
‎በበይነ-መረብ በተደረገው በዚሁ ውይይት ላይ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችን ፣ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) እና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
Recent News
Follow Us