News Detail

National News
Oct 17, 2025 37 views

የትምህርት ሚኒስትሩ በጋምቤላ ክልል እየተገነባ የሚገኘውን ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ የደረሰበት ደረጃ ተመለከቱ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በትምህርት ሚኒስቴር ድጋፍ በጋምቤላ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የግንባታ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በምልከታቸው ወቅት እንዳሉት የሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ ግንባታው ከተጀመረ አጭር ጊዜ ቢሆንም የደረሰበት ደረጃ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው በዚሁ ፍጥነት ጥራቱን የጠበቀና ለተማሪዎች አመቺ ተደርጎ ሊገነባ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ሁሉም በሀገራችን የሚኖሩ ልጆች በተቻለ መጠን ተመጣጣኝ ትምህርት፣ እውቀትና ክህሎት ማግኘት አለባቸው ያሉት ሚኒስትሩ ለዚህም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ በበኩላቸው የሞደል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታው ከታሰበው በላይ በፍጥነት እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅም ስራው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል።
ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱን እየገነባ የሚገኘው ናይል ሌችዌ ኮንስትራክሽን እና ውሃ ስራዎች ድርጅት የፕሮጀክቱ ግንባታ 42.1% እንደደረሰ ለከፍተኛ አመራሮቹ ገለጻ አድርገዋል።
በቀጣይም የፕሮጀክቱ ግንባታ በጥራትና በፍጥነት በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ በትጋት እየተሰራ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ቦም ኮት ገልጸዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርትን በፍትሃዊነት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች 31 የሚደርሱ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እያስገናባ ይገኛል።
Recent News
Follow Us