News Detail

National News
Sep 29, 2020 947 views

የ12ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና በተያዘለት ጊዜ ለመስጠት ትምህርት ቤቶች ኮቪድ-19 መከላከል መሰረት ያደረጉ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ የ12ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲሰጥ በቅድሚያ ትምህርት ቤቶች ኮቪድ-19 መከላከልን መርህ ባደረገ መልኩ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ከፈተናው አስቀድሞም የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት የማረጋገጥ ስራ በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚሰራም ተገልጿል።

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እና ምዝገባ በኦንላይን እንደሚካሄድ እና ተማሪዎች የ45 ቀን የማካካሻ እና የቴክኖሎጂ መለማመጃ ጊዜም እንደሚሰጣቸው ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት እና ፈተናዎችም የሚሰጡት ትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ማሟላት ሲችሉ ብቻ መሆኑም ተገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ ያቅስመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሸራረፉ እንዲተገበሩ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥሪ አቅርቧል።

Recent News
Follow Us