News Detail
Jun 30, 2025
33 views
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን አበረታቱ።
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው የከስዓት በኋላ ፈተና አሰጣጥ ሁኔታን ተዘዋውረው በመመልከት ተፈታኝ ተማሪዎችን አበረታተዋል።
በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፈተና አስተዳደር ሥርዓቱ ከሥርቆትና ኩረጃ ነፃ ለማድረግ ባለፉት ዓመታት በተሰራው ስራ ለውጥ መምጣቱን በመጥቀስ ተማሪዎች በራሳቸው በመተማመን ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ ምክር ለግሰዋል።
በኩረጃ የሚያልፍ ተማሪ ለራሱም ለሀገሩም አይበጅም ያሉት ሚኒስትሩ ከዚህ በኋላ በዚህ መንገድ የሚገኝ ውጤት አለመኖሩ ግልፅ እየሆነ መጥቷልም ብለዋል።
በዚህም ጠንክሮ ያጠናና የሰራ ተማሪ የተሻለ ውጤት እንደሚያገኝ በመግለፅ ለተማሪዎች መልካም ውጤትን ተመኝተዋል።
በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከ608 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናቸው በወረቀትና በበየነ መረብ እንደሚወስዱ መገለፁ ይታወሳል።