News Detail

National News
Jun 30, 2025 54 views

የ2017 ዓ.ም. 12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በመላ አገሪቱ በይነ መረብና በወረቀት ከዛሬ ጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል።

ክብርት ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ ፈተናውን በአዲስ አበባ አስጀምረዋል።፡
ክብርት የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰጠ የሚገኘውን ፈተና በአብርሆት ቤተ መጻህፍት ባስጀመሩበት ውቅት እንደገለጹት ለፈተናው ተገቢው የቅድመ ዝግጅት ስራ ተሰርቷል፡፡
ተማሪዎች አዲሱን ስርኣት ትምህርት መሰረት በማድረግ መጻህፍት አንድ ለአንድ እንዲደርሳቸው መደረጉን ፣ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በተዘጋጀበት አግባብም ተገቢውን እውቀት እንዲጨብጡ ጥረት መደረጉን ተናግረዋል።፡
ተማሪዎች በአግባቡ መዘጋጀት እንዲችሉና የሚገባቸውን እውቀት እንዲጨብጡ ለማድረግም ከ400 ሺህ ለሚበልጡ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት መሰጠቱንም ፣ ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ አመልክተዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር መምህራን ትርፍ ጊዜያቸውን ጭምር ተጠቅመው ተማሪዎችን ሲረዱ መቆታቸውን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ወላጆችና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችም ተማሪዎችን ሲደግፉና ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸውን ጠቅሰዋል።
ፈተናው በወረቅትና በበይነ መረብ እንደሚሰጥ የጠቆሙት ክረብርት ወ/ሮ አየለች በተለይ ፈተናው በበይነ መረብ መሰጠቱ ስርቆትና ኩረጃን በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ እገዛ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ተማሪዎች ፈተናውን በተረጋጋ ሁኑታ እንዲፈተኑና መልካም እድል እንዲገጥማቸው ተመኝተዋል፡፡
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በበኩላቸው ከዛሬ ጀምሮ በሚሰጠው ብሄራዊ ፈተና በአስተዳደሩ 280 ትምህርት ቤቶች 51 ሺ 259 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ አስታውቀዋል፡፡
የትምህርት ምዘናና እና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው በአገር አቀፍ ደረጃ ከ608 ሺ የሚበልጡ ተማሪዎች በወረቅትና በበይነ መረብ ፈተና እንደሚወሰዱ ጠቁመዋል፡፡
Recent News
Follow Us