News Detail
Mar 06, 2025
89 views
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ግምቢ ከተማ ለሚገነባው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ መሠረት ድጋይ ተቀመጠ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ከተማ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ መሠረት ድጋይ አስቀምጠዋል።
ሚኒስትሩ የግንባታውን ማስጀመሪያ መሠረት ድንጋይ ባስቀመጡበት ወቅትም የኢትዮጵያን ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እየተወሰዱ ካሉ እርምጃዎች ውስጥ አንዱ የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ማሻሻል መሆኑን ተናግረዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች መሠረተ ልማት የተሟላላቸው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመገንባት እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው ይህ ዛሬ የግንባታ ማስጀመሪያ መሠረት ድንጋይ የተቀመጠው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ የዚሁ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል።
የትምህርት ቤቱ ግንባታም በአጭር ጊዜ ተጠናቆ የመማር ማስተማር ስራውን እንዲጀምር ይደረጋልም ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው ደረጃቸው የተሻሻሉና መሠረተ ልማታቸው የተሟላላቸው ትምህርት ቤቶችን መገንባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑን አብራርተዋል።
የዞኑ አመራሮች በበኩላቸው የትምህርት ቤቱ ግንባታ በመጀመሩ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ግንባታው እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።
ከዚም በተጨማሪ ሚኒስትሩና አመራሮቹ በጊንቢ ከተማ በሚገኙት ቢፍቱ ግምቢ እና ሴና ግምቢ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመገኘት ያለውን የመማር ማስተማር ሂደት በመመልከት ተማሪዎችን አበረታተዋል።