News Detail
Dec 25, 2024
75 views
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአገሪቱን እድገትና የህዝቡን ህይወት ለማሻሻል ቅድሚያ ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስገነዘቡ።
ትምህርት ሚኒስቴር ከአርባ ሰባት (47) የመንግስተት ዩኒቨርስቲዎች ጋር በ2017 የሚተገበር ቁልፍ የአፈጻጸመም ውል ተፈራርሟል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በስምምነቱ ወቅተት እንደገለጹት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰሯቸው ምርምሮችና የሚያፈሯቸው ዜጎች አገር የሚለውጡና ከዓለም ጋር ተወዳድረው ማሸነፍ የሚችሉ ሊሆኑ ይገባል።
ዩኒቨርስቲዎች ራሳቸውን ወደ ራስገዝነት እያሳደጉ እድገታቸውንና ቀጣይነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸውም ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ተናግረዋል።
ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የተፈረመው ውል ሃላፊነትና ተጠያቂነትን በማስፈን የትምህርት፣ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ጥራት ለማስጠበቅ እንደሚያስችልም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የትምህርትና የምርምር ጥራትን በማስጠበቅ ብቃትና ጥራት ያለው ዜጋ ማፍራት ግዴታ መሆኑን አውቀው በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም ክቡር ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።
በቁልፍ የአፈጻጸም መለኪያ ስምምነቱ መሠረት ውጤት የሚያስመዘግቡ ተቋማት በበጀት ጭምር የበለጠ የሚደገፉበት፣ ወደ ኋላ የሚቀሩና ዝቅተኛ አፈጻጸም የሚያስመዘግቡት ደግሞ ተጠያቂ የሚሆኑበት እንደሆነ ጠቁመዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በበኩላቸው የቁልፍ ስራዎች አፈጻጸም ውሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሳይንሳዊና ዓለም አቀፋዊ መለኪያዎች ላይ ያተኮረ እድገት እንዲኖራቸው እንደሚያስችል ገልጸዋል።
ስምምነቱ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው የክትትልና ግምገማ ስርዓት እንዲኖርና ዩኒቨርስቲዎች በተልዕኳቸው ላይ አትኩረው እንዲሰሩ እንደሚያደርግም ጠቅሰዋል።
በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርተ ተቋማቱ በገቡት ስምምነት መሠረት ስራዎቻቸውን በየደረጃው በማውረድና ጠንክሮ በመስራት ቀጣይነት ያለው ውጤት ለማስመዝገብ መረባረብ እንዳለባቸው ተናግረዋል።
ስምምነቱን የትምህርት ሚኒስትሩን በመወከል የከፍተኛ ትምህርቶ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አት ኮራ ጡሹኔ ዩኒቨርስቲዎቹን በመወከል ደግሞ የየዩኒቨርስቲዎቹ ቦርድ ሰብሳቢዎችና ፕሬዚዳንቶች ፈርመዋል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024