News Detail

National News
Dec 23, 2024 45 views

የት/ቤቶች ስፖርት ውድድር ለሀገራዊ ስፖርት ውጤታማነት የላቀ ሚና እንዳለው ተጠቆመ።

የ2017 የት/ቤቶች የስፖርት ውድድር ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ ወቅት በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት መሰረተ ልማትና አገልግሎት ዴስክ ሃላፊ አቶ ታየ ግርማ እንደገለጹት የት/ቤቶች ስፖርታዊ ውድድርን ማጠናከር ሳይቻል ሀገራዊ የስፖርት ውጤት መጠበቅ አይቻልም።
በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የነበረው የት/ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር በያዝነው የትምህርት ዘመን በዘጠኝ ቀጠናዎች ተደራጅቶ እየተከናወነ መሆኑን ሃላፊው ገልጸዋል።
በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የውድድር ስፖርቶች ክትትልና ድጋፍ ዴስክ ሃላፊ አቶ ዳንኤል ዳርጌ የት/ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር የተፈጠረውን ሀገራዊ የስፖርታዊ ውጤቶች መቀዛቀዝ ክፍተት ለመሙላት ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
ሚኒስቴሩ ለት/ቤቶች ስፖርታዊ ውድድሮች ትኩረት በመስጠት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ በመፈራረም ወደ ስራ የተገባ መሆኑን ጠቁመው ይሄው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር በት/ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ቦጋለ በበኩላቸው ስፖርቱ በማህበረሰቡ ድጋፍ እንዲያገኝ ሁላችንም በአገኘነው አጋጣሚ ሁሉ የማስተዋወቅ ስራ መስራት ይኖርብናል ብለዋል።
በዘጠኙም ቀጠናዎች የተደለደሉ ሁሉም ክልሎች የአፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ውይይት የተደረገ ሲሆን ከጥቂት ቀጠናዎች በስተቀር የስፖርት ሊጉን ስኬታማ ለማድረግ የአመራር ሚና በሚፈለገው ልክ ባለመሆኑ ይህ ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተጠቁሟል።
Recent News
Follow Us