News Detail
Nov 04, 2020
402 views
የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች ሀብታቸውን ማስመዝገብ ጀመሩ።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የፌደራል የስነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሚያደርገው የፌደራል መስሪያ ቤቶች የሀብት ምዝገባ የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች ሀብታቸውን ማስመዝገብ ጀምረዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር የስነ ምግባር እና የፀረ - ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መስፍን ተፈራ የሀብት ማስመዝገብ አዋጅን እና የተሻሻለው የሀብት ምዝገባና እድሳት መመሪያ ላይ ለሰራተኞቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የምዝገባው አላማ በመንግስት አሰራር ውስጥ ግልፅነትን ለማስፈን መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የምዝገባው ሂደትም እስከ ህዳር 30 የሚቆይ ሲሆን ሰራተኛውም ይህንን ተገንዝቦ ሀብቱን በወቅቱ እና አስፈላጊውን መረጃ በጥንቃቄ በመሙላት ገቢ እንዲያደርጉ አስታውቀዋል።
ሀብታቸውን በወቅቱ ባላስመዘገቡ ሰራተኞች ላይም ቅጣት እንደሚተላለፍ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የሚኒስተር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞቹም የፌደራል የስነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሀብት ማሳወቂያ እና ማስመዝገቢያ ቅፅ ላይ ሀብታቸውን መመዝገብ እና ገቢ ማድረግ ጀምረዋል።
ከዚህ ቀደም ኮሚሽኑ ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የሚመለከታቸው ሰራተኞች ሀብታቸውን ማስመዝገባቸው ይታወሳል።