News Detail

National News
Aug 17, 2024 495 views

የመምህራንን ክብርና አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ

የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሀሮምያ ዩኒቨርስቲ በክረምት መርሃ-ግብር የሚሰለጥኑ መምህራንን ጎብኝተዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት ከሰልጣኞች ጋር ባደረጉት ውይይት መምህርነት ሙያ የተከበረ እና የአንድ ሀገር የእድገት መሰረት በመሆኑ ይህን ታለቅ ሙያ ወደነበረበት ክብር ለመመለስና የመምህራንን አቅም መገንባት ፤ኑሮውን ማሻሻል የግድ በመሆኑ መንግስት ከፍተኛ ትከረት ሰጥቶ አየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው ከደመወዝ ጭማሪ ጀምሮ የመምህራን ባንክ እስከመክፈት የሚደርሱ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። በመምህራኑ የሚከፈተው ባንክ ሙያውንና ኑሮአቸውን ለመቀየር ትልቅ ሚና እንደሚኖረውም ጨምረው ተናግረዋል።
ሰልጣኝ መምህራንም በበኩላቸው በክቡር ሚኒስትሩ መጎብኘታቸው ደስ እንዳሰኛቸው ገልጸው ስልጠናውም ለሙያቸው ትልቅ አቅም እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል። መምህራኑ ጨምረውም በስልጠናው አዳዲስ እውቀቶችን እንደቀሰሙና ቴክኖሎጂን በመጠቀም እንዴት ማስተማር እንሚቻል ጭምር አውቀት ያጉኙበትና ከዘመኑ ጋር የሚሄድ መምህር ለመሆን እንዳነሳሳቸው ገልጸዋል፡
Recent News
Follow Us