News Detail
Aug 12, 2024
1.9K views
የምርምር ሥራዎቻችን ውጤታማ ለማድረግ በ“Thematic Research Fund Management” ላይ የተመሠረተ አደረጃጀት ሊኖራቸው እንደሚገባ ተገለጸ።
ከዩኒቨርስቲዎችና ከአጋር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ለተውጣጡ ም/ፕሬዚደንቶች እና ዳይሬክተሮች በሚሠጠው ሥልጠና ላይ የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሸኔ ባስተላለፉት መልዕክት በዩኒቨርሲቲዎች የሚሠሩ ምርምሮች ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ በ“Thematic Research Fund Management”ን መሠረት ያደረገ አደረጃጀት ሊኖራቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።
ክቡር አቶ ኮራ አያይዘውም ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ የምርምር ሥራዎቻችን ከሃገራዊ የትኩረት አቅጣጫ እና ከዩኒቨርሲቲዎች ልየታና ተልዕኮ ጋር የተጣጣመ አጀንዳ በመቅረጽ እና ከድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የምርምር ፕሮጀክቶች ጋር በማስተሳሰር ከቴማቲክ የምርምር አደረጃጀትንና የፋይናንስ ሥርዓታችን በማጠናከር በውጤት ልንመራው ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ሥልጠናው በከፍተኛ ትምህርት ቴማቲክ ምርምር ምንነትና አተገባበር፣ በInter፣ Multi፣ እና Trans-Disciplinary ምርምር ቡድን አመሰራረት እና ግምገማ፣ እንዲሁም በሃገራዊ፣ ተቋማዊ እና MSC/PhD ምርምር ፕሮጀክቶች ትስስር ዙሪያ በፕሮፌሠር ማሥረሻ ፈጠነ በስፋት ተሠጥቷል። የተለዩት አምስቱ ዋና ዋና የቴማቲክ አጀንዳዎች በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በቴክኖሎጂ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ እና በማዕድን ዘርፍ ላይ ያተኮረ ነበር።
የትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ ዶ/ር ሠራዊት ሀንዲሶ በበኩላቸው ከዚህ ስልጠና ሁሉም ሠልጣኞች በቴማንቲክ ምርምር ላይ ያላቸውን ግንዛቤ በማዳበር የቀጣይ ሥራዎቻቸው የ“Thematic Research Fund Management” አደረጃጀትን በመተግበር የምርምር ውጤታማነትን እንዲያሳድጉ አሳስበዋል።
Recent News
Sep 10, 2024
Sep 17, 2024
Sep 04, 2024
የ33ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ መካሄድ ጀምሯል።
Aug 30, 2024