News Detail

National News
Mar 03, 2023 2.2K views

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ለሚገነባው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ

የካቲት 24/2015 (የትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በ20 ሚሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባው የኦሞራቴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሠረት ድጋይ አስቀመጡ ።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌን ጨምሮ በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲና ሌሎች ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የግንባታው አጠቃላይ ወጪ 20 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ሲሆን ወጪው በደቡብ ክልል መንግስትና ሰዎች ለሰዎች በተሰኘው ግብረ-ሠናይ ድርጅት በጋራ እንደሚሸፈን ተገልጿል ።
የትምህርት ቤቱ ግንባታ ከ1 ዓመት እስከ 2 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደምጠበቅም በመርሃ ግብሩ ተጠቅሷል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
Recent News
Follow Us