News Detail

National News
Feb 21, 2023 1.9K views

ህፃናትን በአፍ መፍቻ ቋንቋ ማስተማር ሚናው የጎላ መሆኑ ተገለፀ።

የካቲት 14/2015 ዓም. (የትምህርት ሚኒስቴር) በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመጠቀም ቀን በዛሬው ዕለት በአለም አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ይገኛል።
ይህንንም በማስመልከት ትምህርት ሚኒስቴር የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ሲምፓዚየም አካሂዷል።
በሲምፖዚየሙ መክፈቻ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን እና የትምህርት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶ/ር ሙሉቀን ንጋቱ ሀገራችን ኢትዮጵያ በቋንቋ ብዝሃነት የታደለች በመሆኑ ያሉንን ቋንቋዎች በአግባቡ አልምቶ ለትምህርት ስራዎች መገልገያ የማድረግ ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።
ተማሪዎችን በአፍ መፍቻ ቋንቋ እና እንግሊዝኛ ቋንቋ ተቀላቅሎ ማስተማሩ ለቀጣይ ክፍል ትምህርት ቀላልነት አስተዋጶው የላቀ መሆኑም በጥናት ተመልክቷል።
በሲምፓዚየሙ ላይ የትምህርት ቋንቋዎች አጠቃቀምን የሚዳስስ ጥናታዊ ጹሁፍ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚሠሩ ስራዎች በግብአትነት እንደሚያገለግልም ተመላክቷል።
Recent News
Follow Us