News Detail

National News
Feb 28, 2023 2.1K views

ለትምህርት ዘርፉ ዕድገት ቁልፍ ሚና ያላቸው አዋጆችና ደንቦች ፀደቁ፡፡

የትምህርት ሚንሰትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ውሳኔው ለትምህርቱ ዘርፍ ዕድገት አንድ ትልቅ ምዕራፍ ነው ብለዋል፡፡
የካቲት20/2015 ዓም.(የትምህርት ሚኒስቴር) የሚኒስትሮች ምክር ቤት የካቲት 20/2015ዓም ባደረገው 17ኛመደበኛ ጉባኤ ስብሰባ ለትምህርቱ ዘርፍ ዕድገት ቁልፍ ሚና እንዳላቸው የታመነባቸው አዋጆችና ደንቦች ላይ ውይይት አድርጎ አጽድቋል፡፡
በመደበኛ ስብሰባው ላይ ውይይት ተደርጎባቸው የጸደቁት ሰነዶች የትምህርትና ስልጠና ረቂቅ ፖሊሲ ፤ የዩኒቨርሲቲ አውቶኖሚ (ራስ ገዝ) የሚደነግግ አዋጅ ፤ በከፍተኛ የመንግስት ተቋማትና ማስተማሪያ ሆስፒታሎች ውስጥ የሚሰሩ አካዳሚክ ቴክኒክ ረዳቶችን ተግባር፣ሃላፊነትና ጥቅማጥቅም ለመወሰን የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ፤ የከፍተኛ ትምህርት ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፣ የምርምር ተቋማትና የኢንዱስትሪ ትስስር ረቂቅ አዋጅ መሆናቸው ተመላክቷል ፡፡
ውሳኔውን አስመልክቶ የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ውሳኔው ለትምህርቱ ዘርፍ እንደ አንድ ትልቅ ምዕራፍ የሚቆጠር በመሆኑ አጠቃላይ ለትምህርት ማህበረሰቡ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በቀጣይም ለጸደቁ አዋጆችና ደንቦች ማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎችን በማዘጋጀት ሙሉ ለሙሉ ወደ ትግበራ ማስገባት እንዲቻል የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና ሥራ አስፈጻሚዎች በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Recent News
Follow Us