News Detail

National News
Feb 17, 2023 2.1K views

ተማሪዎችና ታዳጊ ህጻናት በበይነ መረብ አማካኝነት የሚደርስባቸውን ጥቃት በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተገለፀ

የካቲት 10/2015 ዓም. (የትምህርት ሚኒስቴር) የትምህረት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማትና አጋር ድርጀቶች ጋር በመተባበር በበይነ መረብ አማካኝነት ተማሪዎችና ታዳጊ ህጻናት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር በመድሀኒያለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ
በመድረኩ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ታምሩ በበይነ መረብ ግንኙነት አማካኘነት ጎጂና አስጸያፊ ተግባራት እየተበራከቱ በመምጣታቸው አጠቃቀማችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ጥንቃቄ የሚያሻው መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ተማሪዎችና ታዳጊ ህጻናት የጉዳቱ ሰለባ እንዳይሆኑም ግንዛቤ የመፍጠር ፣ የማሳወቅና የመከላከል ስራዎችን በተቀናጀ መልኩ መከወን እንዳለባቸው ተናግረዋል።
ተማሪዎች የኢንተርኔት አጠቃቀማቸውን ጥንቃቄ የተሞላበት በማድረግ ራሳቸውን ከሚደርስባቸው ጾታዊና ሌሎች መሰል ጥቃቶች መከላከል እንደሚገባቸውም በመድረኩ ተገልጿል።
በበይነ መረብ አማካኝነት የሚደርሰውን ጥቃት በመከላከል ሂደት ወላጆች ጉልህ ሚና መጫወት እንዳለባቸው ተጠቁሟል።
የዩኒሴፍ የህጻናት ጥበቃ በኢትዮጵያ ስራ ሃላፊ የሆኑት ጆላንዳ ቫን ድርጅታቸው በተማሪዎችና ታዳጊ ህጻናት ላይ በበይነ መረብ ግንኙነት አማካኝነት የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል የሚደረጉ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ እና ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል ።
Recent News
Follow Us