News Detail

National News
Feb 17, 2023 2K views

"የ222 ሚሊዮን ህጻናት ህልም እውን እንዲሆን እናግዝ" ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ያቀረቡት ጥሪ

የካቲት 10/ 2015 ዓም. (የትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ ዓለም አቀፉ Education can not wait በጠራው የሃብት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ የ222 ሚሊዮን ህጻናት ህልም እውን እንዲሆን እናግዝ ሲሉ ጥሪ አቀርበዋል።
ዓለም አቀፉ Education Can not Wait በጠራው የሃብት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ የተገኙት ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ትምህርትን መምራት በሚለው ርዕስ ላይ የኢትዮጵያን ተሞክሮ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አካፍለዋል፡፡
በንግግራቸው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው ኮቪድ 19፣ ድርቅ ግጭትና ሌሎች ጫናዎችን ተቋቁማ ትምህርትን በማስቀጠል በአሥር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ትምህርት ላይ እንዲቆዩ ማድረግ እንደቻለች አንስተዋል፡፡
ለዚህም ይሆን ዘንድ መንግስት 22 ከመቶ በላይ በጀት ለትምህርት መድቧል ብለዋል፡፡
አንደ Education Can not Wait ሪፖርት በዓለም ዙሪያ 222 ሚሊዮን ህፃናት በተለያዩ ተፈጥሮዓዊና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ከትምህርት ውጭ ወይም በአስቸጋሪ ሁኔታ እንዲማሩ ሆነዋል፡፡
በተጨማሪም 78 ሚሊዮን ህጻናት ወደ ትምህርት ሄደው አያውቁም ።
የኢትዮጵያ ህፃናትን ጨምሮ በዓለም ላይ ወደ 222ሚሊዬን ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ በመሆናቸው ከህልማቸው እርቀዋል ያሉት ሚኒስትሩ ኮንፈረሱ በቅርበት ለመስራትና መፍትሄ ለመፈለግ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህ ሃብት ማሰባበሰቢያ መድረክ የ222 ሚሊዮን ህጻናት ተስፋ እናለምለም በሚል መሪ ቃል 826 ሚሊዮን ዶላር ማሰባሰብ ተችሏል፡፡
Recent News
Follow Us