News Detail

National News
Nov 21, 2022 3.6K views

ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ቤቶችን ደረጃና የመምህራንን ብቃት ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፉ ተጠየቀ

ህዳር 12/2015ዓም (ትምህርት ሚኒስቴር) ከህዳር 8-10 በተካሄደው 31ኛውየትምህርት ጉባኤ የተለያዪ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል ።
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የትምህርት ቤቶችን ደረጃና የመምህራንን ብቃት መለወጥ እንደሚገባ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ(ዶ/ር) ገልፀዋል።
ትምህርት ቤቶች በግብዓት፣ በሂደትና በውጤት ደረጃቸውን በማሻሻል ጥራት ያለው ትምህርት ከቅድመ አንደኛ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ድረስ ለመስጠት ሁሉም ባለድርሻ የድርሻውን ሊወጣ ይገባልም ብለዋል።
የሀገሪቱ አቅም በሚፈቅደው ልክ የመምህራንን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ጀምሮ ብቃታቸውን ለማሻሻል በትኩረት መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል ።
ዩኒቨርሲቲዎችም በየአካባቢያቸው ያሉ ትምህርት ቤቶችን በመደገፍ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ ማድረግ አለባቸው ያሉ ሲሆን የመምህራንን አሰለጣጠን በማሻሻል ጥራት ላይ ማተኮር እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
Recent News
Follow Us