News Detail

National News
Nov 21, 2022 3.5K views

'' ትምህርት ለሁሉም ህጻናት '' በሚል መሪ ቃል የ2015 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለምዓቀፍ 10 ኪ.ሜ ሩጫ ተካሄደ።

ህዳር 11/2015ዓም (ትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል ፣ውድድሩ 31ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በተጠናቀቀ ማግስት የተካሄደ በመሆኑ የትምህርት ዘርፋ ልዩ ትኩረት እንዲያገኝ ተጨማሪ እድል የፈጠረ ነው ብለዋል።
ትምህርት ለህጻናት ስለፈለግን ብቻ ሳይሆን ስለሚገባቸው የምንሰጣቸው ነው :- በመሆኑም በረቂቅ የትምህርት አዋጁ ከ1-8 ባለው ክፍል እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆችን ማስተማር ለወላጅም ሆነ አሳዳጊ አስገዳጅ ሆኖ ተቀምጧል ብለዋል ስራ አስፈጻሚዋ ።
የትምህርት ጥራት ቀጣዩ የትምህርቱ ዘርፍ ትኩረት መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ አመለወርቅ ያንንም ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
በጦርነትና በተለያዩ ምክንቶች የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መገንባት የሁሉንም ዜጋ የተባበረ ክንድ እና ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ በሩጫው የታየው አብሮነት ትምህርት ቤቶችን በመገንባትም በኩል እንዲደገም አስታውሰዋል።
ይህንን ታላቅ ሩጫ "ትምህርት ለሁሉም ህጻናት" በሚል መሪ ቃል እንዲካሄድ ላደረገው ዩኒሴፍ ፣ መረጃውን ለህዝብ ለማድረስ ብቸኛ የሚዲያ አጋር ለሆነው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን እንዲሁም ለሌሎች አጋር ድርጅቶችም ምስጋና አቅርበዋል።
22ኛው ታላቁ ሩጫ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ፣የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣የባህልና ስፖርት ሚንስትር ቀጄላ መርዳሳ ፣ሻለቃ አትሌት ኃይሌገብረስላሴ እና ሌሎችም ታዋቂ አትሌቶች በተገኙበት ተካሂዷል።
በዛሬው ዕለት ለ22ኛ ጊዜ በተካሄደው 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ 40,000 ራጮች ተሳታፊዎች ሆነዋል።
በውድድሩም በወንዶች . አቤ ጋሻሁን 1ኛ ፣ሀይለማርያም አማረ 2ኛ ገመቹ ዲዳ 3ኛ በሴቶች ትዕግስት ከተማ 1ኛ መስታወት ፍቅር 2ኛ ፎቴን ተስፋዬ 3ኛ በመሆን የዘንድሮው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሸናፊዎች ሆነዋል።
በዩኒሴፍ ዋና ስፖንሰርነት እና በሌሎች ድርጅቶች ጥምረት '' ትምህርት ለሁሉም ህጻናት ''በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ የተካሄደው የ2015 ዓም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በስኬት ተጠናቋል።
Recent News
Follow Us