News Detail
Oct 13, 2022
2.5K views
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያደረገውን ዝግጅት ጎበኙ
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) ፣ የኦሮሚያ ክልል ትምህር ቢሮ አመራሮች የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ለመስጠት ያደረገውን ዝግጅት ጎብኝተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በጉብኚታቸዉም በፕሮግራማቸዉ መሰረት ዛሬ ለፈተና መግባት የጀመሩ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን አግኝተዉ አናግረዋል፡፡
ፕ/ር ብርሃኑ በጉብኝታቸውም ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዩኒቨርሲቲዎች ያደረጉት ዝግጅት አስደሳች መሆኑን ገልፀዋል።
የፈተናውን ደህንነት፣ያለምንም የፈተና ስርቆትና ኩረጃ ለማካሄድ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን መመልከት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
እስካሁን እየታየ ያለው ውጤትም አስደሳች መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሩ ዩኒቨርሲቲዎችና የተለያዩ የመንግስት ተቋማት እያደረጉት ያለው ጥረቶች ምን ያህል አቅም እንዳለ የሚያሳይና የሚያስመሰግን መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ከጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ አሁን መፈተን ለማይችሉ ተማሪዎች ፈተናውን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
የ2014ዓም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ የመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ዩኒቨርስቲዎች እየገቡ ይገኛሉ።