News Detail
Jan 26, 2022
1.2K views
The Minister of Education, Prof. Berhanu Nega discussed with the Ambassador of the Government of Hungary to Ethiopia, Attila Thomas on free scholarship programs to Ethiopian students.
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የሀንጋሪ መንግስት አምባሳደር ክቡር አቲላ ቶማስ ጋር በነፃ የትምህርት ዕድል ዙሪያ ውይይት አደርገዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር) ከዚህ ቀደም የሀንጋሪ መንግስት ለኢትዬጵያዊያን ይሰጥ የነበረውን የነፃ የትምህርት ዕድል ስምምነት በማስቀጠል የሁለቱን አገራት ወዳጅነት ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
አምባሳደር ክቡር አቲላ ቶማስ በበኩላቸው አገራቸው በሁለተኛ ዲግሪ እና በሶስተኛ ዲግሪ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ነፃ የትምህርት ዕድል ከዚህ ቀደሙ በተሻለ ሁኔታ ቁጥሩን በመጨመር እንደምትሰጥ ገልፀዋል፡፡
የነፃ የትምህርት እድሉ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት እንደሚያጠናክርም በውይይቱ ተነስቷል።
በየአመቱ የሀንጋሪ መንግስት ለኢትዬጵያ ተማሪዎች በሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ የነፃ ትምህርት እድል እንደምትሰጥ ይታወቃል።