News Detail
Jan 05, 2022
307 views
የኢትዮጵያ የስነ-ህንፃ ማህበር የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት በነፃ የዲዛይን ስራውን ሊያከናውን ነው፡፡
የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር በአማራና አፋር ብሄራዊ ክልሎች በጦርነቱ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን በፊት ከነበሩበት ደረጃ የተሻለ አድርጎ መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ስራ የዲዛይን ስራዎችን በነጻ ሰርቶ ለማስረከብ የሀሳብ ቀረፃ እያካሄደ ነው፡፡፡
በዛሬው እለት በትምህርት ሚኒስቴር በተካሄደው የሃሳብ ቀረፃ የምክክር መድረክ ላይ ከ 20 በላይ የስነ ህንፃ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ የስነ-ህንፃ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አማኑኤል ተሾመ እንደተናገሩት የዲዛይን ስራው በርካታ ደረጃዎችን የሚያልፍ መሆኑንና ዘሬ የተጀመረው ስራ የዲዛይኑን ራዕይ የመንድፍ ስራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ራዕይ የመንደፍ ስራው ትምህርት ቤቶችን በተሸለ ድረጃ ለመገንባት ያለመ መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡
የስነ -ህንፃ ማህበሩ በጦርነቱ በተጎዱ አካባቢዎች የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ትኩረት በማድረግ ደረጃውን የጠበቀ ዲዛይን በነፃ ለመስራት መዘጋጀቱን ተገልጿል፡፡
በዲዛይን ስራውም በርካታ ባለሙያዎች ሙያዊ አስተዋፆ እንደሚያበረክቱ የማህበሩ ፕሬዝዳንት አስታውቀዋል፡፡
የዲዛይን ስራውም በቀጣይ እንደ ሀገር በአዲስ መልክ በሚሰሩ ትምህርት ቤቶች ላይም ተግባራዊ እንደሚሆኑ ተነግሯል፡፡
የሀሳብ ቀረፃ የምክክር መድረኩ ላይ ላይ ሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡