News Detail
Dec 06, 2021
1.1K views
"ልህቀትንና ጥራትን መሰረት ለሚያደርጉ የትምህርት ሥራዎች ቅድሚያ ይሰጣል" :- ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር
6ተኛው አገር አቀፍ የሣይንስና ምህንድስና አውደ ርዕይ ቀንን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለአራት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ሥራ ውድድር መርሃ ግብር ተጠናቀቀ።
የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመርሃ ግብሩ መዝጊያ ላይ እንደገለጹት በትምህርት ዘርፍ ልህቀትንና ጥራትን መሰረት በማድረግ ለሚሰሩ ሥራዎች ቅድሚያ ትኩረት እንደሚሰጥ ገልፀዋል።
የአገራችንን የትምህርት ጥራት ችግር ከቅደመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሰረታዊ በሆነ መልኩ ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ የታዩት የፈጠራ ሥራዎች ውጤት ለነገው ተስፋ ሰጪ መሆኑን በመጥቀስ በትምህርት ሥራም ይበልጥ ጥራት ላይ ማተኮር እንደሚገባ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ተናግረዋል።
በአገር አቀፍ ደረጃ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በሣይንስና ቴክኖሎጂ የሚበቁበት 50 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ሥራ ለመጀመር ዝግጅት መጠናቀቁን ጠቅሰዋል።
በውድድሩ ከ7ተኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ከተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ከስቴም ማዕከላት ለተውጣጡና በሁሉም ዘርፎች የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና መምህራን የመበረታቻ ሽልማቶች ተበርክተዋል፡፡
መርሀ ግብሩን የትምህርት ሚኒስቴር ከ ስቴም ማዕከላት፣ ከዩኔስኮ፣ ከዝቅተኛ የመማር ብቃት (MLC) ጋር በጋራ በመሆን አዘጋጅቶታል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024