News Detail
Dec 01, 2021
1.1K views
የትምህርት ሚኒስቴር ወደ ግንባር ለሚዘምቱ በጎ ፍቃደኛ ዘማቾች ሽኝት አደረገ።
ከትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የተውጣጡ 32 በጎ ፍቃደኛ ዘማቾች በዛሬው እለት ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
ለመከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ እና የስንቅ ዝግጅትም እየተደረገ ነው።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) እርስ በእርስ እንዳንተማመን ያደረገን ስርዓት ጊዜው አብቅቶ "ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም" ለማድረስ በሙሉ አቅማችን ወደ ስራ የምንገባበት ጊዜ ተቃርቧል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ወደ ቀደመ ክብሯ እስክትመለስ ድረስ ለመከላከያ ድጋፋችን እንቀጥላለን ያሉት ሚኒስትሩ እስከ አሁን ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መሰብሰቡን ተናግረዋል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ፒ ኤች ዲ) ማንኛውም ጠላት ጥቃት ከመክፈቱ በፊት ሁለት ሶስቴ እንዲያስብ አድርገን ለጠላት ትምህርት መስጠት አለብን ብለዋል።
ዘማቾቹ በድል እንዲመለሱ በመመኘት የባንዲራ ርክክብ ተከናውኗል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024